1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

ድህነትና የቅንጦት ቤተ መንግሥት በኢትዮጵያ

ሰኞ፣ ግንቦት 21 2015

ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ቀደም ሲል ወደ አገሪቱ ይጎርፍ የነበረው የውጭ ምንዛሪ ፣በጦርነቱ ሳቢያ ተቋርጦአል፡፡ በውጭ አገር የሚኖሩትም የአገሪቱ ልጆች ዶላሩንና ዩሮውን ወደ ኢትዮጵያ ማስተላለፉን „አኩረፈው“ እነሱም ቧንቧውን ዘግተዋል፡፡ኑሮ ተወዶአል፡፡ ጥራጥሬዎች በአንድ ምሽት ብቻ ጨምረው ዋጋቸው አይቀመስም፡፡

https://p.dw.com/p/4Rw4l
Äthiopien Addis Abeba | Hauptstadt will Migration  minimieren
ምስል Seyoum Getu/DW

ድህነትና የቅንጦት ቤተ መንግሥት በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ግዲያ መፈናቅልና ስደት ድርቅና ረሃብ አሁንም ቀጥለዋል።፡ጦርነት በአንድ አካባቢ በረድ ሲል ፣በሌላ የአገሪቱ ክፍል ይቀጣጠላል፡፡በዋናው ከተማ -በአዲስ አባባ ውስጥ ደግሞ በኑሮ ውድነትና በዋጋ ግሽበት አብዛኛው ሠራተኛ ፣ቀጣዩ ዘገባ እንደሚለው ተስፋ የቆረጠበት ደረጃ ላይ ደርሶአል፡፡ በተለያዩ  አካባቢዎች  ተዘዋውራ ሁኔታውን በቅርቡ የተመለከተችው የዶቼቬለዋ ዘጋቢ አንትየ ዲክሀንስ እንዳለችው ብዙዎች በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም ላይ የነበራቸው ተስፋም ተሟጧል፡፡አንዳንዶቹ ሕይወታቸውን ለመግፋት ጫማ ይጠርጋሉ፤ሌሎቹ ጋዜጣ ይሸጣሉ፤የተቀሩት ደግሞ መጽሓፍ ተሸክመው ይዞራሉ፡፡በግንባታ ሥራም ላይ የተሰማሩት ሰዎች ደግሞ ቁጥራቸው ፣እዚያ አዲስ አበባ እጅግ ብዙ ነው ይባላል፡፡
ቡና በጀበና
እዚያው ቆልታ፣እዚያው ፈጭታ፣እዚያው ወቅጣ፣አፍልታ መንገድ ዳር የምትሸጠው ሴት ጥራ ደክማ እሷም ለፍታ በመጨረሻው የምታገኘው ገንዘብ ለምኑም እንደማይበቃት አምርራ ትናገራለች።እዚያና እዚህ የፎቅ ቤቶች በከተማው በአዲስ አበባ ይገንቡ እንጂ የሰሜኑ ጦርነት ፈንድቶ የሕንጻ ቁሳቁሶች ዋጋ ሰማይ ላይ እንዲወጣ .ነጋዴዎች እንደሚሉት ያ ሁኔታ ትልቅ አስተዋዕጾ አድርጎአል፡፡ከዚያም በላይ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ቀደም ሲል ወደ አገሪቱ ይጎርፍ የነበረው የውጭ ምንዛሪ ፣በጦርነቱ ሳቢያ ተቋርጦአል፡፡
በውጭ አገር የሚኖሩትም የአገሪቱ ልጆች ዶላሩንና ዩሮውን ወደ ኢትዮጵያ ማስተላለፉን „አኩረፈው“ እነሱም ቧንቧውን ዘግተዋል፡፡
ኑሮ ተወዶአል፡፡ እንደሚታየው ትላንት ሃምሣና ሰማንያ ብር የሚያወጡ ጥራጥሬዎች- በአንድ ምሽት ብቻ ዋጋቸውን ጨምረው ዛሬ ከፍ ብለው አድረው ሌላ ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡
ዱሮ እንደምንም ብለው ጋዜጣና መጽሔት የሚያነቡ ሰዎችም ፣አሁን ጋዜጣ ሻጩ፣አቶ ገብረ መድህን ሓብሬ -አዛውንቱ አንደአሉት „…እነዚህ ሰዎች ጋዜጣ ገዝተው ከማንበብም ከተቆጠቡ ወራቶች አለፈዋል፡፡“
„አንድ ቀን ለእኔ እና ለልጆቼ ጥሩ ቀን ይመጣ ይሆናል…“  ብለው የሚያስቡት አዛውንት .ተስፋቸውን ቆርጠዋል፡፡“ 
ከእሳቸውም ጋር አብዛኛው የከተማው ኑዋሪ እንደዚሁ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ „ ተስፋቸውን ቆርጠው እርማቸውን አውጥተዋል…“
አንትየ ዲክሀንስይልማ ኃይለ ሚካኤል 
ኂሩት መለሰ 

Äthiopien Stadt Nekemit | Premierminister Abiy Ahmed mit Vertretern der Wollega-Zonen Region Oromia
ምስል Facebook.com/Office PM Ethiopia
Äthiopien Coronavirus l Straßenverkauf - Mutter versorgt Familie
ምስል Solomon Muchi/DW

ማንንተጋፍቶት ስለሺ